Image

ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አመሰራረት

ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የተመሰረተው  በስራ ፈጣሪው በአቶ ከተማ ከበደ አማካኝነት በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 1980 በአነስተኛ ኢንተርፕራይዝነት ነበር፡፡ድርጅቱ ሲመሰረት በአነስተኛ ቢሮ ውስጥ የእርሻ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክና በምትካቸው አገር ወስጥ የሚፈለጉ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ስራ የጀመረ ሲሆን ባለቤቱም እንደ ስራ መሪም እንደ ስራው ዋና አንቀሳቃሽ በመሆን ድርጅታቸውን መርተዋል፡፡

ድርጅቱም እንደማንኛውም አገር በቀል ድርጅት በአንድ ሰው ብቻ ስራዎችን ያከናውን የነበረ ሲሆን ከዚያም ወደ  ዘርፈ ብዙ ትልቅ ኩባንያነት ተሻገረ፡፡

ድርጅቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት ወደ ኩባንያነት ተቀይሮ በ1985 ኬኬ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ በሚል ስያሜ ተደራጀ፡፡ ድረጅቱም በሰው ሃይል እና በሚያስፈልጉ ግብአቶች ተጠናክሮ ወደ አምራች ዘርፍ በማደግ በ1992 የአቃቂ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የብርድልብስ ማምረቻ የነበረውን አንድ ክፍል ከመንግስት በመግዛት ወደ ኢንዱስትሪ የተቀላቀለ ሲሆን በ1993 ተጨማሪ ዘመናዊ ማሽኖችን ከአውሮፓ በማስመጣት ከፍተኛ የማምተት አቅም ያላው አዲስ የብርድልብ  ፋብሪካ አስገንብተዋል፡፡ የብርድልብስ ፋብሪካውም የተለያዩ ዲዛይን ያላቸውን ብርድልብሶች እያመረተ ይገኛል፣በ1995 በዚሁ ቦታ ላይ ተጨማሪ የአክሪሊክ ክር ማቅለሚያ ፋብሪካ በመትከል ማምረት እና ማከፋፈል ጀመረ፡፡  በተለይ በአክሪሊክ ፋብሪካው ከፍተኛ የማምረት አቅምና በነበረው ከፍተኛ የክር ገበያ ፍላጎት የተነሳ ኩባንያው በአጭር ጊዜ እምርታ ሊያሳይ ቻለ፡፡

ኩባንያውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እየሰፋ የመጣ ሲሆን የኩባንያው ባለቤት ተጨማሪ የንግድ ሥራ ዘርፎችን በመክፈት በየዘርፉ ብቁ ባለሞያዎችን በመቅጠር ኩባንያውን ማሻሻል ቀጠሉበት፡፡ ኩባንያውም በብቁ ማኔጅመንት እና የቦርድ አባላት እየተመራ ስራዎችን በቅልጥፍናና ጊዜውን በሚመጥን ቴክኖሎጂ እንዲደግፍ ተደረገ፡፡

በዚህም የተነሳ ኩባንያው  ባለፉት 25 አመት ውስጥ ተስፋፍቶ ከተሰማራባቸው  የስራ ዘርፎች በጨርቃ ጨርቅ ማምረት፣የአክሪሊክ ክር ማቅለም በተጨማሪ በሃገራችን ውስጥ በከፍተኛ እጥረት የነበረውን ከባድ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ችግር ለማቃለል በመጀመሪያ በርካታ ኒሳን ዩዲ ገልባጭ መኪናዎችን በማስመጣት በመቀጠል ከቻይናው ሳኒ ግሩፕ ጋር ውል በመዋዋል ዋና ወኪል በመሆን ከባድ የሆኑ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ለገበያ ያቀርብ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የትራንዚት አገልግሎት በመክፈት የኩባንያውን ገቢና ወጪ እቃዎችን በኩባንያው የትራንዚት አገልግሎት ማሰራት የቻለ ሲሆን ከዚህም ጎን ለጎን የተለያዩ ድርቶች የትራንዚት አገልግሎት ይሰጥ ነበር፡፡

በሪል ስቴት ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ባላቸውን ባለሞያዎች በመታገዝ ግንባታዎች እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በጨው በረንዳ G+5 ግንባታው ያለቀ ህንፃ፣ ሜክሲኮ ሚቼል ኮት አጠገብ 5+G+B+23ቅይጥ አገልግሎት ህንፃ በግንባታ ላይ የሚገኝ በማስገንባት ላይ ይገኛል፡፡

ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በ2008 ጀምሮ የውጭ ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ሲሆን በአለም አቀፍ የጥራት ደረጃን የጠበቁ ቡና፣ጥራ ጥሬ እና የቅባት እህሎችን ወደ አውሮፓ፣ሰሜን አሜሪካ እና ወደ እስያ እየላከ ይገኛል፡፡

ከቅርብ አመት በኃላ በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሰማርቶ የሚገኝ ሲሆን፡፡ኩባንያው በአሁኑ ወቅት፡-

  • በአክለሪክ ክር ማቅለም እና ማከፋፈል
  • በብድልብስ እና ጨርቃ ጨርቅ አምራችነት
  • በሪል ስቴት ልማት
  • በውጭ ንግድ ዘርፍ ቡና፣ጥራ ጥሬ እና የቅባት እህሎችን ወደ ውጭ መላክ
  • በአስመጪ እና አከፋፋይነት
  • በትራንስፖርትና ትራንዚት አገልግሎት

ዘርፎች በመንቀሳቀስ ለብዙ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠርና ለሀገራችን እድገት ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመሆን በንግዱ ዘርፍ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ኩባንያውም የሀገሪቱ ትልቅ ባንክ በሆነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ ደንበኛ ምድብ ውስጥ የተካተተ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ኩባንያውም ማህበራዊ ግዴታውን በመወጣት ረገድ በሀገራችን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካደረጉትና ከሚ ያደርጉት ተርታ የሚመደብና በሥራ አፈፃጸም ከተለያዩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተለያዩ ሜዳሊያዎች ተሸላሚ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Management Members 

ኦመር ዓሊ
ኦመር ዓሊ ዋና ሥራ አስኪያጅ
ቦጋለ ማሞ
ቦጋለ ማሞም/ዋና ሥራ አስኪያጅ(አገልግሎት)
አያሌው አዲሱ
አያሌው አዲሱም/ዋና ሥራ አስኪያጅ(ኦፕሬሽን)
ስለሺ ጨቡድ
ስለሺ ጨቡድፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ