ዋናው መ/ቤት
እንኳን ደህና መጡ
ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የተመሰረተው በስራ ፈጣሪው በአቶ ከተማ ከበደ አማካኝነት በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 1980 በአነስተኛ ኢንተርፕራይዝነት ነበር፡፡ድርጅቱ ሲመሰረት በአነስተኛ ቢሮ ውስጥ የእርሻ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክና አገር ወስጥ የሚፈለጉ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ስራ የጀመረ ሲሆን ባለቤቱም እንደ ስራ መሪም እንደ ስራው ዋና አንቀሳቃሽ በመሆን ድርጅታቸውን መርተዋል፡፡
ድርጅቱም እንደማንኛውም አገር በቀል ድርጅቶች በአንድ ሰው ብቻ ስራዎችን ያከናውን የነበረ ሲሆን ከዚያም ወደ ዘርፈ ብዙ ወደሆነ ትልቅ ኩባንያነት ተሻገረ፡፡
ድርጅቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት ወደ ኩባንያነት ተቀይሮ በ1985 ኬኬ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ በሚል ስያሜ ተደራጀ፡፡ ድረጅቱም በሰው ሃይል እና በሚያስፈልጉ ግብአቶች ተጠናክሮ ወደ አምራች ዘርፍ በማደግ በ1992 የአቃቂ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የብርድልብስ ማምረቻ የነበረውን አንድ ክፍል ከመንግስት በመግዛት ወደ ኢንዱስትሪ የተቀላቀለ ሲሆን በ1993 ተጨማሪ ዘመናዊ ማሽኖችን ከአውሮፓ በማስመጣት አዲስ የብርድልብ ፋብሪካ አስገንብተዋል፡፡ የብርድልብስ ፋብሪካውም የተለያዩ ዲዛይን ያላቸውን ብርድልብሶች እያመረተ ይገኛል፣በ1995 በዚሁ ቦታ ላይ ተጨማሪ የአክሪሊክ ክር ማቅለሚያ ፋብሪካ በመትከል ማምረት እና ማከፋፈል ጀመረ፡፡ ተጨማሪ
ኬኬ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ
አክሪሊክ ክር ማቅለም
ብርድልብስ ማምረት
የውጭ ንግድ
Creating
Happy Individuals
explorers and theatre singers. We
approach work and play with curiosity
and experimentation.
በአጣዬና አካባቢው ለደረሰው ጉዳት መልሶ ማቋቋሚያ ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ደጋፍ ተደረገ
ኩባንያችን በአማራ ልማት ማህበር አስተባባሪነት በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬና አካባቢው ለደረሰው ጉዳት መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን የ20 ሚሊየን ብር 60 ሺህ ቆርቆሮና ብርድ ሰጥተዋል ድጋፉም የወደሙ 1 ሺህ 500 መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል ነው፡፡