ማኅበራዊ ኃላፊነት

ኩባንያችን ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት  ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ በአሁን ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ያለውን የኮረና ቫይረስ ለመከላከል ከህብረተሰቡ ጎን በመሆን ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

COVID-19

ኩባንያችን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከማህበረሰባችን ጎን በመሆን  ይህንን ቫይረስ ለመከላከል የቅድመ ጥንቃቄ ንፅህና መጠበቂያ/Sanitizer/ እና በአነስተኛ ኑሮ ውስጥ ለሚገኙ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

ለሜሪ ጆይ የልማት ማህበር

በሜሪ ጆይ ድጋፍ ለሚደረግላቸው ሀጻናትና አረጋውያን የሚውል 1,000,000 /አንድ ሚሊዮን/ ብር ድጋፍ አድርጎዋል፡፡

ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር

ለከተማ አስተዳደራችን ስር ለሚገኘው ለበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እርዳታ አሰባሳቢ አስር ሺህ/10,000/ ብርድልብስ ስጦታ አበርክቶዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 እና 07 ውስጥ ለሚገኙ በአነስተኛ ገቢ ላላቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የስንዴ ዱቄት፣ ዘይትና ፓስታ አበርክቶዋል፡፡

ለመርሐቤቴና ለአለም ከተማ ወረዳዎች

ለመርሐቤቴ አካባቢ ለሚገኙ ከሶስት ለማያንሱ ወረዳዎች በብር መቶ ሃምሳ ሺህ የሚያወጣ ብርድልብስ ፤ሳኒታይዘር እና የንፅህና መጠበቂያ አበርክቶዋል፡፡
Image

ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳዎች

ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳዎች በብር ሃምሳ ሺህ የሚያወጣ ሳኒታይዘር እና የንፅህና መጠበቂያ አበርክቶዋል፡፡